Monday, January 20, 2014
Tuesday, January 7, 2014
“የራሷ እያረረባት የሰው ታማስላለች”
“የራሷ
እያረረባት የሰው ታማስላለች”
“ጉድ ሳይሰማ
መስከረም አይጠባም” አለ ያገሬ ሰው ይህንን ማሳሌያዊ አነጋገር እዚህ ቦታ ላይ ያምክንያት አላመጣሁትም። ሰሞኑን የሰማሁት ነገር
ገርሞኝ ነው። የወቅቱ የዓለም መነጋገሪያ ጉዳይ ያው እንደምታውቁት የደቡብ ሱዳን ጉዳይ ነው። በሁለት የደቡብ ሱዳን ብሄረሰቦች መካከልየተጀመረው አሰቃቂ ጦርነት፣ የወቅቱ
መነጋገሪያ አጀንዳ የሆነበት በቂ ምክንያት አለ።
ካንድ ጎልማሳ
እድሜ ያላነሰ ፍልሚያ ከሰሜኑ ሱዳን መንግስት ጋር ሲያደርጉ ቆይተው፣ ከብዙ የደም መፋሰስ ስቃይ በኋላ በተባበሩት መንግስታት፣
ባፍሪካ አንድነትና በመሳሰሉት ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ያላሰለሰ ጠረት ሳቢያ ነጻነታቸውን ሊገኙ ችለዋል፡፡ ከዚያ ሁሉ እገዛ በኋላ
ለዚህ ድል በመብቃታቸውና፤ ድፍን የአለም ህዝብ እሰይ አሁን የዚህ ህዝብ ስቃይ አበቃ ብሎ ትንሽ እንኳን ሳያገግም፣እንደገና ወደከፋ
የደም መፋሰስ መግባታቸው እጅግ የሚዘገንን ሁኔታ ነው ።
ሌላ የውጭ
ጠላት ሳይመጣባቸው እርስ በርሳቸው ብቻ በመባላት እንዲህ ያለውን አሳዛኝ እልቂት ሊፈጽሙት ችለዋል። ይህን ችግርም ማቆምም እጅግ
በጣም ውስብስብ እንደሆነ እየተስተዋለ ነው። ለምን ቢሉ፣ ጦርነቱ የሚካሄደው ጎሳን መሰረት አድረጎ ስለሆነ፤ በሁለቱም ብሔር ወይም
ጉሣዎች ዘንድ የሚጥለው ጠባሳ ትንሽ የሚባል አይደለም።
Sunday, January 5, 2014
ብሔርተኝነትና መዘዙ
ብሔርተኝነትና
መዘዙ
መቼም ሁላችንም
እንደምናውቀው አንድ ብሔር ሊወለድ የሚችለው ከአንድ ሰው ነው የዛን
ሰው የዘር
ግንድ ይዘን ስንቆጥር መድረሻችን አንድ ሰው ወይም ሁለት ጥንዶች ጋር ያደርሰናል ። አዳምና ሄዋን እንዲሉ…
ለዚህ እንደምሳሌ
ሊሆነን የሚችለው ሁላችንም የምናውቀው የእስራኤል ሕዝብ ታሪክ ነው፡፡ እሱን እንመልከት እስራኤል የሃገር ስም ሣይሆን የያዕቆብ
ስም ነው፡፡ እርሱ የወለዳቸው አስራ ሁለት ልጆቹ ነገድ ወይም ብሔር ለመሆን በቁ፡፡ የኛንም ታሪክ ስንመለከት ልክ እንደዛው ነው፡፡
ለምሣሌ ስለ ኦሮሞ ብናነሳ ኦሮሞ የብሔር ስም አይደለም የሰው ስም እንጂ እርሱ የወለዳቸው እነ ሜጫና ቱለማ ሲወልዱ ሲዋለዱ በዙ
ተባዙ ታላቅ ህዝብም ለመሆን በቁ፡፡ ለዚህም እንዴት እንደበቁ ለማወቅ አንድ በአንድ እንመርምር ቢባል በቂ የታሪክ ምስክርና አሻራ
እናገኛለን ። መነሻዬ ማን ማንን ወለደ የሚለውን መርምሮ ለማሳየት
ሳይሆን የብሄርንና የጎሳን መዘዝ መጠቆም ነውና ወደ ተነሳሁበት ርዕስ ልመለስ፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)