Sunday, June 29, 2014

የመቐለ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ተከለከለ! – አብርሃ ደስታ

ህወሓቶች የመቐለ ህዝብ ዓፈናውን በሰለማዊ ሰልፍ እንዳያሰማ ለማፈን ያህል የነገው የመቐለ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ከልክሏል። በደብዳቤ እንዲያሳውቁን በጠየቅነው መሰረት የደብዳቤው ይዘት ምን መሆን እንዳለበት ለስድስት ሰዓት ያህል ከተወያዩ በኋላ እነሆ ቀኑና ይዘቱ አዛብተው ሰጥተውናል። ስህተት አለው ስንላቸው፤ ዝም ብላቹ ያዙ እሱም በስንት መከራ ነው ብለውናል። ባጭሩ የተቀመጠው ምክንያት ክልላዊና ከተማዊ ዝግጅት ስላለን አይመችም፤ በቂ የፀጥታ ኃይልም የለንም የሚል ነው። ግን ነገ ምንም ዝግጅት እንደሌለ አረጋግጠናል። በቂ የፖሊስ ኃይል እንዳለም የታወቀ ነው። ንፁሃን ዜጎች ለመደብደብና ለማሳሰር ፖሊስ ያላጡ ለሰለማዊ ሰልፍ ኃይል የለንም እያሉን ነው። ደሞኮ ለሚፈጠር ችግር ሓላፊነት ትወስዳላቹ ብለው አስፈርመውናል። ሌላ ደግሞ የፎርም ችግር እንዳለ ፅሑፉ ያትታል። የምን ፎርም መሆኑ አይታወቅም። ለማንኛውም ሰልፉ ለመከልከል ፈልገው በደብዳቤው የሚፃፍ ምክንያት ማጣታቸው ነው የሚያሳየው። ደብዳቤው ለህዝብ እንበትነዋለን ስላልናቸው ‘ሌላ ግዜ የምንፈቅድ መሆኑን እናሳውቃለን’ ይላል ደብዳቤው። ባጠቃላይ ግን ህወሓት የመቐለ ህዝብ ድጋፍ እንደሌለው እንዲጋለጥ አልፈገምና ከልክሎታል። ጨቋኝ ስርዓት የህዝብ ድጋፍ የለውም። የህዝብ ድጋፍ እንደሌለው እንዲታወቅ ግን አይፈልግም። ሰልፉ ሌላ ግዜም ቢሆን ይደረጋል። ለነገ ግን የመቐለ ህዝብ ሰለማዊ ሰልፍ የመውጣት መብቱ መነፈጉ ግልፅ ሆኗል።

መዝገቦቹ መልሰው ተቀራረቡ የእምነት ክህደት ቃል በኃይል አስፈርመዋቸዋል

መዝገቦቹ መልሰው ተቀራረቡ
የእምነት ክህደት ቃል በኃይል አስፈርመዋቸዋል
ጽዮን ግርማ
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በስድስቱ ጦማሪያንና በሦስቱን ጋዜጠኞች ላይ የፌደራል ፖሊስ የተለያየ ምክንያት እየሰጠ ቀጠሮ የሚያራዝመውን ሁለት መዝገብ አንዴ ሲያቀራርበው መልሶ ደግሞ ሲያራርቀው ቆይቶ አሁን ደግሞ መዝገቦቹን መልሶ አቀራርቧቸዋል፡፡እስረኞቹ ራሳቸውን መከላከል በማይችሉበት ኹኔታ ፖሊስ ያረቀቀውን የእምነት ክህድት ቃል ተገደው እንዲፈርሙ አድርጓቸዋል፡፡
የሦስቱ ብሎገሮች አቤል ዋበላ፣በፍቃዱ ኃይሉና ማኅሌት ፋንታሁን ቀጠሮ ለዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2006 ዓ.ም እንዲቀርቡ የሚል የነበረ ሲኾን ከጠዋት ጀምሮ ችሎቱን ለመታደም የመጣውን ቤተሰብ፣ጓደኞቻቸው፣ጋዜጠኞች፣ዲፕሎማቶችና የወጣቶች ደጋፊዎች በአጠቃላይ ወደ ሦስት መቶ የሚጠጋ ሰው ከችሎት ውስጥ የሚሰማውን አዲስ ነገር ለመጠበቅ በግቢው ውስጥ ቆመው ነበር፡፡ ከጠዋቱ አራት ሰዓት አካባቢ የእስረኞቹ ጠበቃ አቶ አመኃ መኮንን ተጠርተው የመዝግብ ቤት ጸሐፊዋ ስለሌለች ችሎቱ ለከሰዓት በኋላ እንደተዛወረ ይነገራቸዋል፡፡ እርሳቸውም ችሎቱን ለመከታተል ለቆመው ሰው መልዕክቱን ያስተላልፋሉ፡፡ ጥቂት ሰዎችም ይህን መልዕክት ሰምተው ግቢውን ለቀው ይወጣሉ ብዙኃኑ ግን እዛው እንደቆሙ መጨረሻውን ለማየት መጠባበቅ ይጀምራሉ፡፡

ኢትዮጵያዊው-ኖርዌጂያን ኦኬሎ ኦካይ ኦቻላ ”ሞት ሊበየንበት ይችላል” -በሽብርተኝነት ክስ ሞት ተፈርዶባቸው ሞታቸውን የሚጠባበቁ 127 ሰዎች ኣሉ

በኖርዌይ ሃገር ውስጥ በኖርዌጂያንኛ የሚታተመው ዳግብላደት የተባለው ጋዜጣና ድረ-ገጽ ”ኢትዮጵያዊው-ኖርዌጂያን” ኦኬሎ ኦካይ ኦቻላ በሚቀጥለው ሳምንት ሞት ሊበየንበት ይችላል” ሲል ኣውጥቶኣል።
”ባለፈው ሳምንት ለማወቅ እንደተቻለው ዕድሜው 52  የሆነና  ኦኬሎ ኦካይ ኦቻ  የተባለ ኖርዌጂያን ኢትዮጵያ ውስጥ በሽብርተኝነት ተከሶ በእስር ላይ ይገኛል።” tiltalt for terror በማለት የጀመረው የኖርዌዩ ዳግብላደት ሲቀጥልም…”የኢትዮጵያ መንግስት ቃለ ኣቀባይ እንደሚለው ገንዘብ ኣሰባስቦና ኣጥቂ ቡድን መልምሎ ኣደጋ ለማድረስ ሲሞክር ያዝነው በማለት መከሰሱን ያትትና በበኩላቸው የኖርዌዩ የሰብኣዊ መብት ጥበቃም ሆኑ የዓለም ኣቀፉ ሰብኣዊ መብት ተሟጋቾች ድርጊቱን በጥብቅ ያወገዙት ሲሆን፣ ኣያይዘውም ለዚሁ ድረ-ገጽ ታሳሪው ግለሰብ ያለበት ሁኔታ ከወትሮው የከፋ እንደሆነም ስጋታቸውን እንደገለጹለት ያወሳል።

 ኢትዮጵያንም ሆነ የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት፣ በኣሁኑ ወቅት በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ውስጥ የሚገኙትን  ኦኬሎ ኦካይ ኦቻ ”በሚገባ ያውቃሉ” ያሉዋቸውን የሰብኣዊ መብት ተሟጋችና ኖርዌጂያን ፈሊክስ ሆርነ ን  ኣነጋግሮ ድረ-ገጹ ያገኘው መልስ ”ኖርዌጂያኑን ኦኬሎ በሚቀጥለው ሳምንት የሚሰየመው ችሎት ሞት ሊበይንበት ይችላል” በማለት የገለጹ ሲሆን ኣክለውም፣
”በሃገሪቷ ውስጥ በሽብር ወንጀል የሚከሰሱት ዜጎች የሚገጥማቸው የሞት ፍርድ ነው። ነገር ግን እነዚህ ሞት የሚፈረድባቸው ዜጎች ምንም ማስረጃ ያልቀረበባቸው ናቸው። በሽብር ክስ ስለተከሰሱ ብቻ ዕድላቸው ይሄው ነው። በሞት ቀጠና የሚገኙትን ዜጎች የሚዘግበው ዓለም ኣቀፉ ድርጅት በኢትዮጵያ በእስር ቤት ውስጥ በሞት ቀጠና (ሴል) የሚሰቀሉበትን ወይም የሚገደሉበትን ጊዜ የሚጠባበቁ 127  ዜጎች  ይገኛሉ ሲል ፈሊክስ ሆርነ ለድረ- ገጹ ገልጸዋል።
 ሌላው ኣምነስቲ ኢንተርናሽናል ውስጥ የሚሰሩት ጌራልድ ካዶርድ ”የኢትዮጵያ መንግስት ኦኬሎን እንደከሰሰው በሽብር ወንጀል ጦር ሲመለምልና ሲያደራጅ ኣግኝቶት ከሆነ፣ የሞት ቅጣት ይበይኑበታል የሚለው ስጋቴ ነው።የፍርድ ሂደቱን እንደምናየው የሞት ቅጣቱ በፍርድ ቤቱ ይለወጣል የሚል ዋስትና የለንም።” ኣያይዘውም ባለፈው ዓመት 8 ጋምቤላ ውስጥ ያሉ የተቃዋሚ ድርጅት ኣባላቶች በሽብርተኝነት ከሰዋቸውና የሞት ፍርድ በይነውባቸው ሞታቸውን በመጠባበቅ ላይ ናቸው።”
 ጭፍጨፋ
ኦቻላ ከሽብርተኛ ጋር ግንኙነት እንዳለው ኣላውቅም። ነገር ግን በጋምቤላ ውስጥ መንግስትን የሚቃወም ጠንካራ ተቃዋሚ ድርጅት የለም። መንግስትን ለመቃወም የሚነሱትንም ሽብርተኛ የሚል ስም በክልሉ መንግስት ይለጠፍባቸዋል።
 ኦቻላ የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት የነበረ ጊዜ፣ massakre 13. desember 2003. የ 1000 በላይ  የኣባወራዎች መኖሪያ ቤቶች በገዥው ስርዓት ወታደሮች ሲቃጠልና ከ400 የኣኙዋክ ንጹሃን ተወላጆች በጥይትና በስለት ሲታረዱ በስፍራው  ነበር። ይሄንንም ተከትሎ ወደ ደቡብ ሱዳን ስልጣኑን በመተው መሰደዱንና ከዚያም ከቤተሰቡ ጋር  በኖርዌይ ”ትሮንዳሄም” በተባለ ቦታ  በስደተኝነት በመግባትና ፈቃድ ጠይቆ በ2009 ዓ.ም የኖርዌጂያን ዜግነት ተሰጥቶት ነበር።
  ቢሆንም  ከ 2012 ጀምሮ በጋምቤላ ውስጥ በሚከናወነው ሁኔታዎች ይረበሽ ነበር። በዚህም የተነሳ ወደዚያው ኣቅንቶኣል።ማድረግ ግን ኣልነበረበትም።በኣንድ ወቅት በክረምት ወራት የሱዳን የመረጃና ደህንነት ሰራተኞች በሱዳን ጁባ ውስጥ ያለን ኣንድ ሆቴል በድንገት ከበቡት። ከዚያም በውስጡ የነበሩትን የሱን ጓደኞች  ኣስረዋቸው ወደ ኢትዮጵያ  ልከዋቸዋል በማለት ድረ- ገጹ ኣትቶኣል።
ቶርቸር
በኣሁኑ ሰዓት ኦኬሎ በእስር ቤት ውስጥ ባልተረጋገጠ መረጃ ውስጥ ይገኛል። ይህ ኖርዌጂያን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ማወቅ ኣይቻልም።በኢትዮጵያ ውስጥ በሽብርተኝነት በእስር ቤት ውስጥ ሆኖ  የእናትነት እንክብካቤን ማግኘት ህልም ነው።እስረኞች ለቶርቸርና ስቃይ የተጋለጡ  መሆናቸውን ፈሊክስ ሆርነ  ለድረ-ገጹ ኣስረድተዋል።
የኦኬሎን የፍርድ ሁኔታ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኘው ሪፖርተር የተሰኘው  ጋዜጣ ችሎቱ  ጁላይ 1 ይውላል ብሎ ቢገልጽም፣ የእኛ Dagbaldet በሲዊድን ያለውን የኢትዮጵያ ኣምባሳደር ለማግኘት ሞክረን ያልተሳካልን ሲሆን፤ ዓለም ኣቀፉን የሰብ ኣዊ መብት ተሟጋች ድርጅትንም ሆነ በኣዲስ ኣበባ ካለውም የኖርዌይ ኤምባሲ ትክክለኛ የችሎት ጊዜውን ማረጋገጥ ኣልተቻለም።
የኖርዌይ የውጭ ጉዳይም ለኣንድ ኣዲስ ኖርዌጂያን በኣደጋ ውስጥ በሚሆንበት ጊዜ፣ ወይም ኣደጋ በገጠመው ወቅት እንዴት መከላከል  እንዳለበት ከድረ- ገጹ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ መስጠት ኣልፈለጉም።ድረ- ገጹ   ምላሽ በማጣቱም ይመስላል በኮንጎ ውስጥ ኖርዌጂያዊው Joshua French  በሞት ሲቀጣና፣  Shahid Azim  በኣስገድዶ መድፈር ወንጀል ፖኪስታን ውስጥ ተይዞ ሞት ሲፈረድበትም ኣላስጣሉትም በሚል ኣጣቅሰው ያለፉት። ቢሆንም ይላሉ የውጭ ጉዳይ ቃል ኣቀባይ ፍሮደ ኣንደርሰን፥ እስከኣሁን ከተከሳሹ ስለ ፍርድ ውሳኔውንም  ሆነ  ስለ ችሎቱ ቀን የምናውቀው የለም በማለት ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ያለው የኖርዌይ ኣምባሳደር  ኦኬሎ ኦካይ ኦቻላን በተመለከተ ተደጋጋሚ  ጥያቄዎችን ለኢትዮጵያ መንግስት ኣቅርቦኣል። ኦኬሎ ያለበትን ሁኔታ፣ የፍርድ ሂደቱን ለመከታተልና በእስር ቤት ለመጎብኘት፣ ቢሆንም  ከኢትዮጵያ መንግስት ምንም  ምላሽ  ኣልተገኘም። የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ሁኔታውን በኣደገኛነት እንደሚያዩትም ሳይገልጹ ኣላለፉም።
ባለፈው ሳምንት  የኦኬሎ ባለቤት ኦባ ኦድዋ ኦመት kona Obo Adwo Omot fram i Dagbladet  ”… ባለቤቴ ሽብርተኛ ሳይሆን የፖለቲካ እስረኛ ነው” በማለት ገልጻ ነበር። ይህችው የ ኣራት ልጆች እናት የሆነችው ባለቤቱ ባለፈው ሳምንት እንደገለጸችው፣ ”…በኣሁኑ ሰዓት በዚህ ጠባብ ክፍል ከኣራት ልጆቼ ጋር እገኛለሁ። ምንም የማውቀው ነገር የለም። ባለቤቴም የሚያውቀው ነገር የለም። የኖርዌይ መንግስት የተቻለውን ሁሉ ኣድርጎ ባለቤቴን ከእስር እንዲያስወጡልኝ እማጸናለሁ በማለት ነበር የገለጸችው።

Friday, June 27, 2014

ለውጭ ዜጎች ቅምጥ የሆኑ ሴቶች እና ሴተኛ አዳሪ አግብተው የሚኖሩ ወንዶች


ሰላማዊት ከበደ (ስሟ ተቀይሯል)፡፡ በሁለት ዓይነት የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ትገኛለች፡፡ ቤት ተከራይቶ ያስቀመጣትና የሚረዳት የውጭ ዜጋ ወጣት አለ፡፡ በሌላ በኩል አፈቅረዋለሁ የምትለው ሌላ ኢትዮጵያዊ ጓደኛም አላት፡፡
ዕድሜዋ አሥራ ዘጠኝ እንደሆነ፤ ከፍቅረኛዋ ጋር ከሦስት ዓመት በላይ አብረው መቆየታቸውን ትናገራለች፡፡ እሷ እንደምትለው ከውጭ ዜጋው ወዳጇ ጋር ከተገናኙ ከአንድ ዓመት በላይ ሆኗል፡፡
ታላቅ እህቷ የውጭ ዜጋ ወዳጅ ነበራት፡፡ በዚህም በተደጋጋሚ ወደ ውጭ ትመላለስ ነበር፡፡ ደህና ሊባል የሚችል ገንዘብም ነበራት፡፡ ቤተሰባቸው በጣም ችግረኛ የሚባል ያልነበረ ቢሆንም የታላቅ እህቷ ከውጭ ዜጐች ጋር ወዳጅነት በመመሥረትና ገንዘብ ማግኘት የቤተሰባቸውን ይሁንታ አግኝቶ ነበር፡፡ ዛሬም ታላቅ እህቷ የአንድ የውጭ ዜጋ ቅምጥ ስትሆን ሐበሻ የወንድ ጓደኛም አላት፡፡ በዕድሜ የገፋው (ሰባ ዓመት) የውጭ ዜጋ ወዳጇ ሕልፈተ ሕይወትን እሷም ፍቅረኛዋም በጉጉት እንደሚጠባበቁ በተለያየ ጊዜ በግልጽ ስትናገር ትደመጣለች፡፡

Thursday, June 26, 2014

የወያኔን የጥፋት ድግስ እናምክን



ኢትዮጵያን የሚገዛው ጉጅሌ ሀገራችንን እየወሰደበት ያለው አደገኛ አቅጣጫ አሳሳቢ ከመሆን አልፎ የአደጋውን 
መራራ ፍሬ ማየት ከጀመርን ሰነበትን። የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ወሳኝ ከሆነው የወደፊቱ የጋራ ጥቅማቸውና 
ህልውናቸው በበለጠ 
ልዩነታቸውና ያለፈ ታሪካቸው እንደዋናው ነገር እየተቆጠረ ለሚሰበከው ስብከት የኢትዮጵያ ህዝብ አስተዋይ ባይሆን 
ኖሮ እስካሁን ብዙ ጥፋት 
በደረሰ ነበር።

ቅዳሜ: የመቐለ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ይካሄዳል!

ዓረና መድረክ ቅዳሜ ሰኔ 21, 2006 ዓም በመቐለ ከተማ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ያካሂዳል። ለሰልፉ የሚሆን ሙሉ ዝግጅት ተጠናቋል። የመቐለ ህዝብ በሰልፉ ለመሳተፍ ተዘጋጅቷል። ቅዳሜ ጥዋት ከአምስት ሺ በላይ ህዝብ ይሳተፋል ተብሎ ይጠበቃል።
ሰልፉ የጠራንበት ዋነኛ አጀንዳ መድረክ በአዲስ አበባና በክልሎች ዋና ከተሞች እያደረገው ካለው የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ አካል ሲሆን የሰልፉ ዋነኛ አጀንዳዎች ደግሞ የፍትህ እጦት፣ የነፃነት እጦት፣ የዉሃ ችግር፣ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፣ የመሬት ጉዳይ፣ የግብር ጉዳይ፣ የማዳበርያ ጉዳይ ወዘተ ናቸው።
ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትም ሰለማዊ ሰልፍ በማድረግ ይረጋገጣል። የትግራይ ህዝብ እስካሁን ድረስ ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቱ ተነፍጎ ይገኛል። በአላማጣ፣ ኲሓ፣ አይናለም፣ መቐለ (ገፊሕ ገረብ)፣ ሓውዜን፣ ዓዲግራት ወዘተ ዜጎች ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ መክረው በፌደራል ፖሊስ ተደብድበዋል፣ ታስረዋል፣ ተገርፈዋል፣ ተገድለዋል። ስለዚህ ቅዳሜ ጥዋት ሰለማዊ ሰልፍ የሚጀመርበት ታሪካዊ ቀን ይሆናል። በመቐለ ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ የተፈቀደ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ይደረጋል ማለት ነው።
ስለዚህ የመቐለው የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ከዉሃ ጥያቄ የዘለለ ነው። የዉሃ ጥያቄ አንድ መሰረታዊ ጉዳይ ሁኖ ሌሎች አስቸኳይ መፍትሄ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች አሉ። ሰዎች በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች እየተገደሉ ነው። በሌሎች ክልሎችም እየተገደሉብን ነው። ንፁሃን ዜጎች ያለ ፍርድ እየታሰሩ፣ በድንጋይ እየተወገሩ፣ በፖሊስ እየተደበደቡ፣ በመርማሪዎች እየተገረፉ፣ ያለ ምንም ወንጀል በሽብር እየተከሰሱ ነው። ከዚህ በላይ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ የሚጠይቅ ጉዳይ የለም።
ከሰብአዊ መብት ጥሰት፣ ከመገረፍ፣ ከመታሰር፣ ከመገደል በላይ ምን ሊያደርጉን ይችላሉ? በሌሎችስ ከዚህ በላይ ምን ተደረገ? ስለዚህ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ በቂ ምክንያት አለን። የመቐለ ህዝብ ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቱ በሰለማዊ ሰልፍ ማክበር አለበት። የመቐለ ህዝብ እንደነ አዲስ አበባዎች፣ ባህርዳሮች፣ ደሴዎችና ሀዋሳዎች የተቃውሞ ሰልፍ የማድረግ መብቱ ሊከበርለት ይገባል።
የመቐለ ህዝብ ነፃነት ይፈልጋል። ስለዚህ ይሰለፋል። የቅዳሜ ሰልፍ በገዥው መደብ ካልተስተጓሆለ በቀር ኃይለኛ ሰልፍ ይደረጋል። በአደባባይ ስለሚደረግም ማንም ሰው አይቶ ይመሰክራል። የትግራይ ህዝብ የህወሓት ደጋፊ እንዳልሆነ ያስመሰክራል። ፎቶዎችና ቪድዮች እንቀርፃለን። ትመለከታላቹ።
ሰልፉ ቅዳሜ ጥዋት በ3:00 ሰዓት ከአደባባይ ዘስላሴ (ባዛር) ተነስቶ በሓውዜን አደባባይ አልፎ ሮማናት አደባባይ አቋርጦ አብርሃ ካስትል ሆቴል ከደረሰ በኋላ ወደ ናሽናል ሆቴል ታጥፎ በጤና ጣብያ በኩል ላዕለዋይ ፍርድቤት ደርሶ ሮማናት አደባባይ ላይ ይጨረሳል። የመድረክ መሪዎች ንግግር ያደርጋሉ። በ6:00 ሰዓት ይጠናቀቃል።
ህወሓት የሀዋሳውን፣ የባህርዳሩን፣ የአዲስ አበባውን ወይ የደሴውን ያህል ከፈቀደልን የቅዳሜ ሰልፍ በእርግጠኝነት የተዋጣለት ይሆናል። እስቲ ህወሓት ለትግራይ ህዝብ ሰልፍ ከፈቀደ እንይ። መቐለ ሰልፍ ልትጀምር ነው። ህዝብ ዓረና መድረክ ያለውን ድጋፍ ባደባባይ የሚገልፅበት ቀን: ቅዳሜ።
ህወሓት ሰልፉ እስኪጠናንቀቅ ድረስ ፀጥታ ካስከበረ ህወሓትን በፅሑፍ ነው የምናመሰግነው። ምክንያቱም የትግራይ ህዝብ እንደሌላው ህዝብ ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቱ አስከብሮለታል ማለት ነውና። ሰለማዊ ሰልፍ መፍቀድ በራሱ ጥሩ ነገር ነው። ሰልፍ ለትግራይ ህዝብ ተአምር ነውና። ምክንያቱም ተፈቅዶልን አያውቅም።
እስቲ ህወሓት ትፈተን። እስቲ ህወሓት የህዝብ ድጋፍ አለኝ ብሎ የሚተማመን ከሆነ ሰልፉ እስኪጠናቀቅ ድረስ ሰልፉን ለማየት ዝግጁ ይሁን።
ለማንኛውም ቅዳሜ እንገናኝ። የዉስጥ ለውስጥ ቅስቀሳው አልቋል። ነገ ዓርብ ፎርማል ቅስቀሳ ይደረጋል።

Wednesday, June 25, 2014

በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብትን የደፈጠጡ አገር አልባ ናቸው!

በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ወንጀል ፍፃሜ መሪ ተዋንያን ሆነው ከቆዩ በኋላበመሰደድ በአሜሪካ እራሳቸውን ደብቀው በተቀመጡ የሰብአዊ መብትደፍጣጮች ላይ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የፍትህ መምሪያ ጥቆማእንዲቀርብለት ኢትዮጵያውያንን/ትን በማበረታታት ላይ ይገኛል፡፡
እነዚህ በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን የፈጸሙ ጨካኞች በሰው አገር ሄደው ተደብቀዋል፡፡ እነዚህ ወንጀለኞች በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በበማታለል  ገብተው ለ30 ዓመታት ተደብቀዋል፡፡ እነዚህ በሰው ደም የተዘፈቁ ወንጀለኞች በቀላሉ ሊያዙ በሚችሉበት አገር በመሄድ ለድፍን ሶስት ዓመታት የተደበቁም አሉ ፡፡
እነዚህ የሰብአዊ መብት ደፍጣጭ ወንጀለኞች ከኒዮርክ እስከ ሎስአንጀለስ ባሉ ታላላቅ ከተሞች እራሳቸውን ደብቀው ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ የፉኝት ዘሮች ማንም አይነካንም በሚል የእብሪት ስሜት ህዝብ በሚሰበሰብባቸው የአደባባይ ቦታዎች እና በእምነት ተቋማት ሳይቀር ደረታቸውን ገልብጠው ይንፈላሰሳሉ፡፡ በየቡና ቤቶች እና ምግብ ቤቶች ሲወጡ ሲገቡ ይውላሉ፡፡ በጎዳናና በመንደር መንገድ ላይ ይንፏቀቃሉ፡፡ የተማሩም አሉባቸው ያልተማሩም አሉባቸው፡፡ በስልጣን ላይ በነበሩባቸው ጊዚያት የዘረፏቸውን ገንዘቦች በውጭ ባንኮች አጭቀዋል፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የንግድ ተቋማትን በማንቀሳቀስ ንብረት አፍርተዋል፡፡ ሌሎቹም  ኑሯቸውን ለመምራት እና ዓላማዎቻቸውን ለማሳካት የአገልግሎት ሰራተኞች ሆነው ህይወትን በችግር መግፋት ላይ ይገኛሉ፡፡ ከንጹሀን የግፍ ሰለባዎች ጋር የሞት ዋስትና ተፈራርመዋል፡፡ ንጹሀን ዜጎችን ጨፍጭፈዋል፣ አስጨፍጭፈዋል፣ ረሽነዋል፣ አስረሽነዋል፣ ገድለዋል፣ አስገድለዋል፣ ፈጅተዋል፣ አስፈጅተዋል፡፡

Tuesday, June 24, 2014

ከሕገ-መንግሥቱ በፊት


ትናንት ሰኔ 14 ቀን 2006 ዓ.ም ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹ያገባኛል ባይነት እና ጋዜጠኝነት በአምባገነን ሥርዓት ውስጥ›› በሚል ርዕስ እኔን ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ እና ዳዊት ሰለሞንን የውይይት መነሻ እንድናቀርብ በጋበዘን መሰረት በእኔ በኩል ለውይይት መነሻ ሀሰብ ይሆናሉ ብዬ ያቀረብኋቸውን ሶስት ነጥቦች እንዲህ አቅርቤያዋለሁ፡፡

በመጀመሪያ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ጉዳይ ‹‹ያገባኛል ባይነት እና ጋዜጠኝነት በአምባገነን ሥርዓት ውስጥ›› በሚል ርዕሥ የውይይት መነሻ ሀሳብ ከሙያ አጋሮ ቼ ጋር እንዳቀርብ ስለጋበዘኝ በቅድሚያ ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡




የሕገ­መንግሥቱ አንቀጽ 29

ነሐሴ 15 ቀን 1987 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ­መንግሥት ሲጸድቅ የፈረሙበት የወቅቱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ነበሩ፡፡ ይህ ሕገ­መንግሥት በአንቀጽ 29 (1) እና (2) ላይ ሃሳብን በነጻነት የመገለጽ መብትን በተመለከተ እንዲህ ይላል፡­
‹‹ማናኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የመሰለውን አመለካከት መያዝ ይችላል፡፡ ፣ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሐሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው፡፡ ይህ ነጻነት በአገር ውስጥም ሆነ ውጪ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሑፍ ወይም በሕትመት፣ በሥነ­ጥበብ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ፣ በማንኛውም ዓይነት መረጃና ሐሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነጻነቶችን ያካትታል፡፡››
ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ ከጓደኛዬ አቤል ዓለማየሁ ጋር ‹‹ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት?›› በሚል ርዕስ ለንባብ ባበቃነው መጽሐፍ ውስጥ ይህን ሕገ­ መንግሥት አስመልክቶ ዶ/ር ነጋሶን ቃለ መጠይቅ በማድረግ አነጋግረናቸው ነበር፡፡ ከላይ በመግቢያዬ የጠቀስኩት አንቀጽ 29 መከበር አለመከበሩ ከጥያቄዎቼ መካከል አንዱ ነበር፡፡ ዶ/ር ነጋሶም እሳቸው በምላሻቸው እንዲህ አሉ፡­

Sunday, June 22, 2014

አንድነት ፓርቲ በአዋሳ ሊያደርገው የነበረው ሰልፍ አመራሮችንና አባላትን በማሰር ከተማዋን በፀጥታ ኃይሎች በመውረር ተደናቀፈ

በዛሬው ዕለት በአዋሳ ከተማ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በሀዋሳ ከተማ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ በቅስቀሳ ላይ የነበሩ የፓርቲው አባላት ከሐሙስ ዕለት ጀምሮ እስከ ትላንት ድረስ ከ30 በላይ በፖሊስ የታሰሩ ሲሆን የሲአን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለገሰ ላንቃሞ ለምን ይታሰራሉ ብለው በመጠየቃቸው እሳቸውንም አስረው ከምሽቱ 3፡30 ለቀዋቸዋል፡፡ በቅስቀሳው ወቅት ወረቀቶች የተበተኑ በመሆኑ ህዝብ በነቂስ ሊወጣ እንደሚችል ስጋት ያደረባቸው የደህዴን ካድሬዎች ትላንት ማታ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ተጨማሪ 7 የአንድነት የሀዋሳ አመራሮችና አባሎች በቁጥጥር ስር አውለዋል፡፡ የደቡብ ክልል የደህዴን ካድሬዎች ከተለቀቁ ነገ ሰልፉን ከማድረግ ወደኋላ አይሉም በሚል ለሁለት ተከፍለው ሲሟገቱ ማምሸታቸውንና አቶ መንድሙ ወታንጎ የተባሉት የደህንነት ኃላፊ መፈታት የለባቸውም መፍታት እንኳን ካለብን የሰልፉ ሰዓት ካለፈ በኋላ ነው በማለታቸው በእስር ቤት እንዲያድሩ መወሰኑና በዛሬውም ዕለት የሀዋሳ ከተማ በፀጥታ ኃይሎች ከፍተኛ ጥበቃ ሥር መሆኗን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገልፀዋል፡፡
ሳም ቮድ ሶን's photo.
ሳም ቮድ ሶን's photo.

በሺህ የሚቆጠሩ አማሮች አማራ በመሆናቸው ብቻ ተመርጠው ከምዕራብ ወለጋ ከጊምቢ እና ቄሌም (እንፍሌ ወረዳ አሽ ቀበሌ) ተፈናቀሉ


ጉዳያችን

 14/2006 ዓም (ጁን 22/2014)

በብዙ ሺህ የሚቆጠር የአማራ ህዝብ ኢትዮጵያውያን ከምዕራብ ወለጋ ጊምቢ እና ቄሌም በኃይል አካባቢውን እንዲለቁ ከመደረጉ በላይ ድብደባ እና ግድያ እንደተፈፀመባቸው ቪኦኤ የአማርኛው አገልግሎት ሰኔ 12/2006 ዓም ምሽት ባስተላለፈው ዘገባ ገለፀ።
ዘገባው የተፈናቃዮችን ምስክርነት እንዳስደመጠው ድብደባው እና ግድያው በከተማው ሕዝብ እና ፖሊስ የታገዘ መሆኑን እና ህይወታቸውን ያተረፉት በኮርኒስ እና ጫካ በመደበቅ መሆኑን ሲገልጡ፣አንድ ምስክርነታቸውን ለቪኦኤ የሰጡ ተፈናቃይ አክለው እንደገለፁት ከጊምቢ ከተማ ብቻ ከሶስት ሺህ በላይ የአማራ ህዝብ ኢትዮጵያውያን መፈናቀላቸውን ተናግረዋል።ሌላው ምስክርነት ሰጪ ደግሞ ቁጥሩን ከስምንት ሺህ ሕዝብ በላይ አድርሶታል።

አምስት ልጆች የነበራቸው መሆናቸውን የተናገሩት ሌላ ተፈናቃይ የነበራቸው መደብር መዘረፉን እና ካለምንም ሀብት መቅረታቸውን፣ጉዳዩን አቤት ለማለት ወደ ባለስልጣናት ቢሄዱም ሰሚ ማጣታቸውን አስታውቀዋል።
የቪኦኤ ጋዜጠኛ ጉዳዩን አስመልክቶ ቀደም ብሎ የአካባቢው የፀጥታ ጉዳይ ኃላፊ የተባሉ እሳቸው ግን የኦሕዴድ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ነኝ ያሉ አቶ አወቀ የተባሉ የክልሉ ባለሥልጣን ስለጉዳዩ ሲናገሩ ”ያባረረ የለም’ ሲሉ ተደምጠዋል።

የኦሮምያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳይ ኃላፊ ወ/ሮ ራቢያ ኢሳ ”ሰዎቹ የሄዱት ፈርተው ነው” ካሉ በኃላ ”ቁጥራቸው ”መቶ አይሞሉም ማለታቸው ግርምትን ፈጥሯል።የቪኦኤ ጋዜጠኛ አቶ ሰለሞን በመቀጠል ቁጥሩ አይደለም ወሳኙ አንድም ሰው ቢሆን ለምን ተፈናቀለ? ደግሞስ ምን ያስፈራቸዋል? ያብራሩልኝ ብሎ ለጠየቃቸው ወ/ሮ ራቢያ አጥጋቢ መልስ ለመስጠት ሳይችሉ ቀርተዋል።
የኢህአዲግ/ወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ሕዝቡን በአካል መለብለብ ከጀመረ ሰነበተ።ሺዎች የእዚህኛው ሌሎች የእዚያኛው ብሄር ተወላጅ ናችሁ እየተባሉ ተፈናቅለዋል።በተለይ ከአማራው ህዝብ ተወላጅ የሆኑ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከጉርዳፈርዳ፣ከበንሻጉል፣ከኢልባቦር እና ከወለጋ አሰቃቂ ግድያ እና ድብደባ እየተፈፀመባቸው ለዘመናት ያፈሩትን ንብረት እየተነጠቁ መባረራቸውን ያመለከቱ ዘገባዎች ሲወጡ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።

Saturday, June 21, 2014

ድርብ አኃዝ ዕድገት ወይስ ድርብ ድህነት?


poor1


በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የዓለምአቀፍ ልማት ትምህርት ክፍል ሥር የኢኮኖሚ ጥናት የሚያካሂደው የኦክስፎርድ የድህነትና የሰብዕ ልማት ማዕከል (The Oxford Poverty and Human Development Initiative (OPHI)) ሰሞኑን ባወጣው የ2014 የጥናት መረጃ ደሃ ከሚባሉት አገራት ዝርዝር ኢትዮጵያ ከመጨረሻው ሁለተኛ መሆኗን ገለጸ፡፡ የጥናቱ ዘገባ ኢህአዴግ በየጊዜው ከሚያቀርበው የዕድገት ስሌት ጋር በግልጽ የሚጋጭ መሆኑ ተነገረ፡፡
በዓለማችን በሚገኙ 108 በማደግ ላይ ባሉ አገራት በየጊዜው ጥናት የሚያካሂደው ማዕከል ጥናቱን በሚያካሂድበት ጊዜ 10 መለኪያዎችን እንደ ግብዓት እንደሚጠቀም ይናገራል፡፡ እነዚህም በሦስት ዘርፎች የተጠቃለሉ ናቸው – ትምህርት፣ ጤና እና የኑሮ ሁኔታ፡፡ በተለይ በኑሮ ሁኔታ ሥር ኤሌክትሪክ፣ ጽዳት፣ የሚጠጣ ውሃ፣ የንብረት ባለቤትነት፣ ወዘተ በግብዓትነት ተወስደዋል፡፡
በዚህ ዓይነት እኤአ ከ2002 እስከ 2011 ድረስ ያለውን መረጃ በማጠናቀር በወጣው ዘገባ መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥ ከ100 ሰዎች መካከል 87ቱ ድሃ ተብለው የሚጠሩ ሲሆን 58ቱ ሰዎች ግን መናጢ ደሃ ተብለው የሚጠሩ መሆናቸውን ይናገራል፡፡ ድህነቱ በገጠር እጅግ የከፋ እንደሆነ በመጠቆም ከ100 ሰዎች ውስጥ 96ቱ ደሃዎች እንደሆኑ፤ በከተሞች አካባቢ ግን ከ100 ሰዎች መካከል 46ቱ ደሃ ተብለው የሚጠሩ መሆናቸውን ያስረዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በአጠቃላይ የአገሪቷ ክፍሎች ከ100 ሰዎች መካከል 31ዱ በቀን ከ20ብር በታች በሚገኝ ገቢ እንደሚኖሩ ጠቁሟል፡፡
ድህነቱ የከፋባቸው “ክልሎች” ብዙም ልዩነት እንደሌላቸው የሚያሳየው የጥናቱ ዘገባ ከሁሉም ግን ሶማሊ በደሃነት ቀዳሚ ነው፡፡ በጥቂት ነጥብ ልዩነት ኦሮሚያ፣ አፋር፣ አማራ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ በቅደም ተከተል ተቀምጠዋል፡፡ በእነዚህ አምስት ክልሎች ከ100 ሰዎች ውስጥ 90 እና ከዚያ በላይ የሚሆኑት ደሆች መሆናቸው በጥናቱ ተዘርዝሯል፡፡
የ108 በማደግ ላይ ያሉ አገራት የድህነት መለኪያ ዝርዝር የያዘው ዘገባ በግልጽ እንደሚያሳየው የመጨረሻዋ ደሃ አገር ኒጀር ስትሆን ከዚያ ቀጥላ ኢትዮጵያ ነች፡፡ እስከ 10 ባሉት የመጨረሻ አገራት ውስጥ ማሊ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ላይቤሪያ፣ ጊኒ፣ ሶማሊያ፣ ቡሩንዲ፣ መካከለኛው አፍሪካ እና ጊኒ ቢሳው ከ3 – 10 ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡
በየጊዜው የኢትዮጵያ ዕድገት “ድርብ አኻዝ” እንደሆነ ለሚናገረው ኢህአዴግ ይህ ዓይነቱ ዓለምአቀፋዊ ዘገባ የከፋ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር በአስተያየት ሰጪዎች ዘንድ ይነገራል፡፡ በተለይ “ምርጫ” እየቀረበ ባለበት ወቅት ይህ ዓይነቱ በታዋቂ ዩኒቨርሲቲ የሚመራ ማዕከል የወጣ የጥናት ዘገባ የሚያመጣው ተጽዕኖ ከፍባለ ሁኔታ ለመጠቀም ተቃዋሚ ፓርቲዎች በቂውን ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባቸው እነዚሁ ወገኖች ይናገራሉ፡፡ ኢህአዴግ የማይስማማውን ማንኛውንም ዓይነት ዘገባ “የልማት ጸሮች” ያወጡት፣ “የአሸባሪዎች እጅ ያለበት”፣ “የኒዎ ሊበራል አቀንቃኞች ዘገባ”፣ “የኪራይ ሰብሳቢዎች ምኞት”፣ ወዘተ እያለ እንደሚያጥላላውና እንደሁኔታው የተለመደውን “ማጣፊያ” በኢቲቪ ወይም ሌሎች ድቃይ “የሚዲያ” ክፍሎች ላይ እንደሚያቀርብ ጎልጉል አስተያየት የጠየቃቸው በኢትዮጵያ የከፍተኛ ተቋም ምሁር ገልጸዋል፡፡
ይህ የኦክስፎርድ ማዕከል ይህንን ጨምሮ በየጊዜው የሚያቀርባቸው የጥናትና ምርምር ውጤቶች በበርካታ ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች፣ በፖሊሲ አውጪዎች እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና ሌሎች ተመሳሳይ ተቋማት ጥቅም ላይ እንደሚያውሉት በድረገጹ ላይ አስታውቋል፡፡
የጥናቱን ዘገባ በPDF ለማግኘት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡ በቀጥታ ከማዕከሉ ድረገጽ ላይ ለማግኘት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡

Saturday, June 7, 2014

የኢህአዲግ/ህወሃት ቁልፍ ተግባር:- አራት ኪሎን መጠበቅ


የኢህአዲግ/ህወሃት ቁልፍ ተግባር:- አራት ኪሎን መጠበቅ

ልብ ብላችሁ ተመልከቱ:: ኢህአዲግ/ህወሃት ስልጣን ከያዘበት “ግንበት” 1983 ጀምሮ የሚፈጽማቸው ነገሮች ሁሉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የሚያልሙት ቤተ መንግስን ለመጠበቅ ያለሙ ናቸው።  ላፍታ ወደ ኋላ ልመላሳችሁ።  ብዙ ሀገሮች ዋና ከተማቸውን የሚመሰርቱበት ቦታ ለሀገራቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ውጭያዊ እና ሌሎች ስትራቴጅ ጠቀሜታዎች የሚያበረክተውን አንድምታ መሰረት በማድረግ ነው። በተለይ የባህር በር ያላቸውን ሀገሮች ስንመለከት ብዙዎቹ ዋና ከተማቸው የባህር በርን የተንተራሰ ነው።  ኢትዮጵያ ረጅም የባህር በር የነበራት ሀገር ነበረች። ከሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብ ምስራቅ (ከአማሴን ሰሜን ጫፍ እስከ ጅቡቲ ደቡባዊ ክፍል) ድረስ በቀጭን መስመር የባህር አዋሳኝነቷን ማጣቷ የኢትዮጵያን ካርታ የሚመለከት ባዕድ እንኳን የሚያጤነው ጉዳይ ነው። ይሄ ለምን ሆነ? የቀደሙ መንግስታት እራሳቸውን ከውጭ ወራሪ በህዝብ ለመከለል ይረዳናል ሲሉ ባላቸው ግንዛቤ እንደሆነ አንድ የታሪክ መምህሬ ክፍል ውስጥ ሲናገር አስታውሳለሁ:: ለእኔም ትርጉም ሰጥቶኛል። እናም ቤተ_መንግስትን ለማስከበር በማሰብ ዘላለማዊ የሀገር ማንነት እና ጥቅምን ወደ ጎን በመተው ዋና ከተማን መሃል ሀገር እና ቤተ ክርስቲያንን ከፍተኛ ቦታ (ኮረብታ) ላይ መመስረት የተለመደ ሆኖ የዘለቀ እውነታ ነው።